በመጋቢት 17፣ 2020፣ የሙልትኖማህ ካውንቲው ሊቀመንበር የሆኑ ዲቦራህ ካፎውሪይ ጊዜያዊ በኮቪድ-19 የተነሳ በሚመጣ የደሞዝ ማጣት ሳቢያ የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻሉ ከመኖሪያ ቤት ማስወጣት ላይ ስለተጣሉ ጊዜያዊ ክልከላዎችን አሳውቀዋል። በዚህ ጊዜያዊ ክልከላ በኩል፣ በዚህ የኢኮኖሚ እና የፐብሊክ ጤና አስቸኳይ ጊዜ ወቅት ብዙ ሰዎች ቤት አልባ የመሆን እጣ ፈንታ እንዳይገጥማቸው ለማድረግ አቅደናል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ውዝግብን ለመቀነስ እና ሰዎች ቤቶቻቸውን እንደማያጡ ማረጋገጥን ለማስቀጠል፣ የካውንቲውን ፖሊሲ ከኦሬጎን በክልል-አቀፍ ከቤት ማስወጣትን በጊዜያዊነት ከሚከለክለው ትእዛዝ ጋር ለማጣጣም በሚያዝያ 16፣ 2020 የካውንቲ ኮሚሽነሮች ቦርድ ተመርጧል።

ያም ለሙልትኖማህ ካውንቲ ውስጥ ላሉ የመኖሪያ ቤት ተከራዮች ምን ማለት እንደሆነ እንደሚከተለው ሰፍሯል፡

outline of a person with a check next to it

  • ከቤት ማስወጣትን በጊዜያዊነት የሚከለክለው ትእዛዝ በካውንቲው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የኪራይ ክፍያ መክፈል ያልቻለን ማንኛውንም የሙልትኖማህ ካውንቲ ነዋሪ ከቤት እንዲወጣ ከመደረግ ይጠብቀዋል።
  •  ለመኖሪያ ቤት ተከራዮች በሌላ በማንኛውም የህግ አላማ ከመባረር አይከላከልላቸውም። 

calendar icon

  • አሳማኝ በሆነ በተቻለ መጠን በፍጥነት መክፈል እንደማይችሉ ለአከራዮ ይንገሩ። 
  •  በመጀመሪያው ወር ወይም ከዚያም በፊት ለአከራዮ የግድ መናገር አይኖርብዎትም። ይህም በሚያዝያ ያለፈበት ማንኛውም ኪራይ ላይ ከበፊት ጀምሮ የሚተገበር ነው።

documents

  •  ደሞዝ ወይም ገቢ ማጣትዎን የሚያሳይ ማስረጃ ለአከራዩእንዲያቀርቡ አይጠበቅብዎትም ።
  • ሁሉንም ሰነዶች ያከማቹ፣ ሆኖም፣ ለማንኛውም ግዛት ወይም ፌደራል ኪራይ ድጋፍ ፕሮግራሞች ብቁ መሆን ይችሉ ዘንድ ነው።

money sign

  • በሙልትኖማህ ካውንቲ ያሉ የመኖሪያ ቤት ተከራዮች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ካበቃ በኋላ አሁንም ቢሆንም የሚከፍሉበት የስድስት-ወር እፎይታ ጊዜይኖራቸዋል።
  • የኪራዩን ክፍያ ጊዜው ሲደር መክፈል የሚችሉ ከሆነ፣ የቤት ኪራዮን መክፈል አለብዎት።

scales of justice

  • አከራዩ ካስፈራራዎት፣ የዘገየ ዋጋ ጭማሪ ካደረገ፣ ወይም ተጨማሪ መመሪያ የሚፈልጉ ከሆነ እንደ የተከራዮች ማህበረሰብ ህብረት ወይም የኦርጎን ህጋዊ እገዛ አገልግሎቶችን አይነት ከማህበረሰብ ግብዓቶች ምክር እና ድጋፍን ለእገዛ ይፈልጉ።
  •  አከራዮች እና የመኖሪያ ቤቶቻቸው ተከራዮች ሁለቱም ወገኖች ፈቃደኛ ከሆኑ ወደ ክፍያ እቅዶች መግባት ይችላሉ። ወደ ክፍያ እቅድ ለመግባት የህግ መስፈርት የለም።