drawing of a woman in a house

በቤት ውስጥ ይቆዩ። ህይወትን ይታደጉ።

በሜይ 7 ቀን፣ አገረ ገዢው ብራውን (Brown) ኦሬገንን (Oregon) ቀስ በቀስ እንደገና የመክፈት አቀራረብን አውጀዋል። ምንም እንኳን አንዳንድ የኦሬገን (Oregon) አካባቢዎች የስራና አገልግሎት መስጫዎች እንደገና እየተከፈቱ ቢሆንም፣ ከተዘጉት በርካታዎች ግን እስካሁን ድረስ ገና አልተከፈቱም። የመልቲኖማህ ካውንቲ (Multnomah County) እጅግ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ጉዞዎች ካልሆነ በስተቀር እቤት መቆዬት ይገባል በሚለው የአገረ ገዢው ትዕዛዝ ስር እንዳለ ይቆያል። ይህ ትዕዛዝ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት የተላለፈ ስቴት-አቀፍ ትዕዛዝ ነው። በዚህ ወቅት፣ እጅግ በተቻለ መጠን እቤት ውስጥ መቆየት የተህዋሱን/ቫይረሱን ስርጭት በመገደብ ህይወትን ያድናል። 

ጤንነትን መጠበቅ

COVID-19ን የሚያመጣው ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ መተላለፍ ይችላል። ጤናማ ሆኖ ለመቆየት፡

 • ጥሩ ስሜት ቢሰማዎም፣ በተቻለ መጠን በቤት መቆየትዎን ይቀጥሉ
 • ውጪ ላይ ከሌሎች ሰዎች እና አብረዎት ከማይኖሩ ሰዎች ቢያንስ 6 ጫማ ያህል ርቀት ይጠብቁ
 • እጅዎን አዘውትረው በመታጠብ እና በሚያስልዎ ጊዜ በመሸፈን  የጀርም ስርጭትን ይከላከሉ
 • ፊትዎን በእጅዎ አይንኩ
 • በተደጋጋሚ በእጅ የሚነኩ ነገሮችን ማፅዳት እና ከጀርም ነፃ ያድርጉ
 • ውጪ በሚወጡ ጊዜ የጨርቅ፣ የወረቀት ወይም አንዴ ተጠቅመው የሚጥሏቸውን የፊት መሸፈኛዎች ይጠቀሙ
 • ከታመሙ፣ በቤት በመቆየት እና በመራቅ ሌሎችን ከበሽታው ይጠብቁ

እንደ ልብ በሽታ፣ አስም፣ የስኳር በሽታ ወይም የደም ግፊት የመሳሰሉ ቀጣይ ወይም ስር ሰደድ በሽታ ካለብዎ፣  COVID-19 እጅግ በጣም ሊያሳምምዎ ይችላል።  ድንገት ቢታመሙ ዕቅድ ለማውጣት ከዶክተርዎ ጋር ይነጋገሩ።

decorative imageህመም ከተሰማዎት

ህመም ከተሰማዎት — በተለይ ከትኩሳት እና ሳል ጋር — በቤትዎ ይቆዩ እና ሌላ ጊዜ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርጉትን ነገር ያድርጉ፡ መተኛት፣ ማረፍ፣ ፈሳሽ በብዛት መጠጣት። ለCOVID-19 የተለየ መድሃኒት የለውም።

የCOVID-19 ምልክቶች ከታየብዎ እና የጤና ምክር ካስፈለግዎ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ደውለው ያግኙ።

ምልክቶቹ የሚያካትቱት፡

 • ሳል
 • የትንፋሽ እጥረት ወይም ለመተንፈስ መቸገር
 • ትኩሳት
 • ብርድ ብርድ ማለት
 • ተደጋጋሚ መንቀጥቀጥ እና ብርድ ብርድ ማለት
 • የጡንቻ ህመም
 • ራስ ምታት
 • ጎሮሮ መከርከር
 • አዲስ የመቅመስ ወይም የማሽተት አቅም ማጣት

የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ መታከም እንደሚገባዎ ወይም እንደማይገባዎ እና እንዴት ሕክምና ማግኘት እንደሚችሉ ይነግርዎታል። አቅራቢ የሌለዎት ከሆነ፣ አቅራቢያዎ ያሉ ማናገር የሚችሏቸውን የክሊኒክ ዝርዝሮች ለማግኘት እንዲሁም ለምርመራ መረጃ ወደ 211 ይደውሉ። በMultnomah County የሚኖሩ ከሆነ፣ በ503-988-5558 ላይ የህብረተሰብ ጤና ማእከሎቻችንን ማግኘት ይችላሉ። የመድህን እና ኢሚግሬሽን መረጃ አያስፈልግም እናም ማንም መክፈል ባይችል አይመለስም።

እንዲሁም ትክክለኛውን ሕክምና ለማግኘት ለCOVID-19 ያሎትን ተጋላጭነት ማወቅ  ይችላሉ። የሚፈልጉትን ቋንቋ ለመምረጥ ከድረ ገጹ ስር “ተጨማሪ ቋንቋዎች” የሚለውን ይጫኑ።

home isolationበቤት ውስጥ መገለል

የCOVID-19 ምልክቶች ከታዩብዎ፣ ከሌሎች ርቀው በቤት ውስጥ በተለየ ክፍል ውስጥ እረፍት ያድርጉ እና ያገግሙ። ከተቻለ፣ የተለየ ሽንትቤት ይጠቀሙ። ምግብ፣ እቃዎች ወይም ፎጣዎችን ከሌሎች ጋር አይጋሩ። በተደጋጋሚ ይታጠቡ እንዲሁም ከጀርም ነፃ ይሁኑ። ከሚከተለው በኋላ በቤት ውስጥ መገለል ሊያቆሙ ይችላሉ፡

 • የተከሰተብዎት ትኩሳት እና ሳል ወይም የትንፋሽ ማጠር (የትኩሳት-መቀነሻ መድሃኒት ወይም የሳል መድሃኒት ሳይጠቀሙ) የመሻሻል ለውጥ ካሳየ ጀምሮ ቢያንስ 3 ቀናት (72 ሰዓታት) ካለፉ።
 • ለመጀመሪያ ጊዜ ህመም ከተሰማዎት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ 10 ቀናት ካለፉ።

graphic of person wearing a maskየፊት መሸፈኛዎች እና የሕክምና ማስኮች

በሸቀጣሸቀጥ መደብር፣ መድሃኒት ቤት ወይም በተጨናነቁ ቦታዎች ከሰዎች 6 ጫማ ርቀት መጠበቅ በማይችሉበት ጊዜ የጨርቅ የፊት መሸፈኛዎችን እንዲያደርጉ CDC ይመክራል።

የጨርቅ የፊት መሸፈኛዎች ርቀትን መጠበቅን ሊተኩ አይችሉም። የጨርቅ የፊት መሸፈኛዎች እርስ በእርስ ለመጠባበቅ ከምናደርጋቸው ነገሮች አንዱ ነው።

ሕብረተሰቡ የሕክምና ጭምብሎችን ወይም N95 መተንፈሻዎችን ማድረግ የለበትም። የጤና እንክብካቤ ባለሞያዎች እነዚህን የሕክምና ጭምብሎች እራሳቸውን ለመጠበቅ እና ስራቸውን ለመስራት ይፈልጓቸዋል።

ቤት መስራት የምንችላቸውን የጨርቅ የፊት መሸፈኛዎች እንዴት እንደሚሰሩ ምስል እና መረጃ ለማየት ከፈለጉ የ CDC ድረ-ገጽ ን ይመልከቱ።

Immigrations and Customs Enforcement (ICE)

ከማርች 18 ጀምሮ፣ ICE ግብረ ሃይሉን ለጊዜው እንደሚያቋርጥ እና በሕብረተሰብ የደህንነት አደጋዎች እና በወንጀል ምክንያት ለአስገዳጅ ቅጣት ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግለሰቦች የሲቪል ኢሚግሬሽን ግብረ-ሃይልን በመፍራት ሕክምና ከመፈለግ ሊቆጠቡ አይገባም።

ማህበረሰባዊ ቅጣት እና COVID-19

ለኮሮናቫይረስ (COVID-19) የሚደረጉ የሕክምና ወይም የመከላከል አገልግሎት በአሜሪካ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለሚጠይቁ ሰዎች እንደ ተፃራሪ እንደማይቆጠር የፌደራል መንግስት አስታውቋል

ለተለያዩ ማግኘት የሚችሏቸው የማህበረሰብ ጥቅማ ጥቅሞች አይነት መረጃ፣ በራስዎ ቋንቋ ለማነጋገር ወደ 211 ይደውሉ። ስለ ማህበረሰብ ጥቅማ ጥቅም እና ቅጣት ልዩ ጥያቄ ካሎት Oregon Law Center/Legal Aid Services of Oregon Public Benefits ቀጥታ መስመር በ 1-800-520-5292 ይደውሉ።

ለበለጠ መረጃ

ኮቪድ-19 ቀላል እውነታዎች

ኮቪድ-19 የመረጃ ገፅ

የፊት መሸፈኛ ጨርቆች ጥቅም (766.72 KB)

ጥያቄዎች?

ወደ 2-1-1 ይደውሉ፣ 7 ቀናት በሳምንት ከጠዋት 8፡00 እስከ ማታ 11፡00 | ወይም 211Info ይጎብኙ