woman at desk with headset making a callመጋቢት 23፣ 2020

የእውቂያ ፍለጋ ማለት የህዝብ ጤና የበሽታዎችን ስርጭትን ለማስቆም የሚጠቀምበት መሳሪያ ነው። የህዝብ ጤና ሰራተኛው የኮቪድ-19 ስርጭትን ለማስቆም የእገዛ ጥሪ በሚያደርግበት ወቅት እርስዎ የሚሰጧቸው መልሶች።

የእውቂያ ፍለጋ እንዴት እንደሚሰራ

የሆነ ሰው በኮቪድ-19 ፖዘቲቭ በሚሆንበት ወቅት ለጤና መምሪያ ሪፖርት ይደረጋል። ፖዘቲቭ ሆኖ የተገኙ ግለሰቦች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ፣ በአቅራቢያቸው ማን እንደነበረ፣ እና የት አካባቢ ለቫይረሱ ተገላጭ እንደሆኑ ለማወቅ እንጠራቸዋን።

ማነው ወደ እኔ የሚደውለው?

የእኛ ቡድን አባላት:

  • በሙልትኖማህ ካውንቲ ጤና መምሪያ ውስጥ እንደሚሰሩ ራሳቸውን ያስተዋውቃሉ
  • የእርስዎን ሃገር ቋንቋ ይናገራሉ እና፣ የማይናገሩ ከሆነ፣ ከአስተርጓሚ ጋር እንሰራለን
  • በዚህ ሰዓት ለማውራት ነፃ ካልሆኑ በኋላ መልሰን እንደውልልዎታለን

ከእኛ ቡድን አባላት ውስጥ ካለ ግለሰብ ሲደወልልዎት አንዳንድ ስሜቶች ሊሰማዎት ይችላል። የእርስዎ ስሜቶች የተለመዱና አሳማኝ ናቸው። ውጤቶቹ ምን ማለት እንደሆኑ መረዳትዎን እናረጋግጣለን። የጤና ድጋፍ እንዴት እንደሚያገኙና በዙሪያዎ ያሉት ሰዎችን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ማወቅዎን እናረጋግጣለን። ከእኛ ጋር የሚጋሩት መረጃ ሚስጥራዊና የተጠበቀ ነው።

የእውቂያ ፈላጊዎች ምን አይነት ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ?

  • ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወዴት እንደሄዱ እና ከማን ጋር የቅርብ ንክኪ እንደነበረዎት እንጠይቃለን። 
  • ስለጤናዎ፣ መኖሪያ ቤትዎ፣ እና ቅጥርዎ እንጠይቃለን። 
  • ደህና ሆነው ለመቆየት እና ለማገገም ምን እንደሚያስፈልግዎት እንጠይቅዎታለን። በቤትዎ ውስጥ ለመቆየት እቅድ እንዲያዘጋጁ ልንረዳዎት እንችላለን።

የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሮች (social security numbers) ወይም የክሬዲት ካርዶች አንጠይቅም። ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ አንጠይቅዎም። ማንነትዎን ከፌዴራል መንግስት ጋር አናጋራም። ከህግ ማስፈፀም ወይም (ኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ማስፈፀም) ጋር የሚገናኝ መረጃን እኛ አናጋራም።

በእኔ መልሶች ምን ታደርጋላችሁ?

የሰጡን መረጃ በሽታው እንዳይሰራጭ ለማስቆም ይረዳናል።

መረጃውን በኮቪድ-19 የመያዝ ስጋት ያላባቸው ሰዎችን ለመፈለግ እና ለማግኘት እንጠቀምበታለን። የእርስዎን መረጃ በሚስጥር እንጠብቃለን። የእርስዎን እስካላገኘን ድረስ ተጋላጭ ያደረጓቸው ሰው ማን እንደሆነ ለእነሱ አንነግራቸውም። አንዳንድ ጊዜ በኢንፌክሽን ተጠቅተው ሳለ የነበሩበት እንደ ስራ ቦታ አይነት ስፍራዎችን ልናሳውቆት ያስፈልጋል። ይህን በአስማማኝ እና በግል ለማድረግ ከእርስዎ ጋር የምንሰራ ይሆናል።

የእኔ እውቂያዎች ምን እንዲያደርግ ይጠይቃሉ?

በኮቪድ-19 ከተጠቃ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ለመጨረሻ ጊዜ ተጋላጭ ከሆኑበት ቀን አንስቶ ለሁለት ሳምንታት ከሌሎች ሰዎች ርቀው በቤተ እንዲቆዩ እንጠይቃለን። 

  • ሰዎች በቤታቸው ደህንታቸው እንደተጠበቀ ይቆዩ ዘንድ ግሮሰሪዎችን እና ሌሎች ግብዓቶች የሚያገኙበትን እቅድ እንዲያገኙ ልንረዳቸው እንችላለን
  • እውቂያዎች በቤት ውስጥ እንዲቆዩ እንጠይቃለን፣ ግን በቤታቸው ካልቆዩ አንቀጣቸውም ወይም ሪፖርት አናደርግባቸውም።
  • ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ከማወቃቸው በፊት ቫይረሱን ሊያሰራጩ ስለሚችሉ ሙሉ ጊዜ በቤት መቆየት አስፈላጊ ነው። 
  • ሰዎች ምልክቶች ካሳዩ የህክምና እንክብካቤ ለመፈለግ እቅድ እንዷሏቸው እናረጋግጣለን።

እባክዎ በምንደውል ወቅት ምላሽ ይስጡ። ኮቪድ-19 ን ለማስቆም የእርስዎን እገዛ ያስፈልገናል።